የኢሬቻ በአልን ምክንያት በማድረግ የስነጽሁፍ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኢሬቻ በአልን ምክንያት በማድረግ የስነጽሁፍ ምሽት በአራት ኪሎ ፕላዛ ተካሄደ::

የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የከተማ፣ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የጥበብ ሰዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት "ኢሬቻ ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ታላቅ የስነጽሁፍ ምሽት በአራት ኪሎ አካሄደ።

በዛሬው እለት የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ የመጣልና ሌሎች ትላልቅ የሀገርን ብልጽግና የሚያረጋግጡ ተግባራት መከናወናቸውን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የኢሬቻ በአል የተራራቀ የሚቀራረብበት፣ የይቅርታ፣ የአብሮነትና የምስጋና በአል መሆኑን ገልጸው ይህንንም መጠበቅና ታሪክንና ባህልን እየዘከሩ ለትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

በቃልና በተለያየ መንገድ የገዳ ስርአት አንዱ አካል ስለሆነው ኢሬቻ ከመግለጽ ይልቅ ኪነጥበባዊ በሆነ መንገድ ማስረዳቱና ታሪክን መዘከሩ ከምንም በላይ አይረሴ እንደሚያደርገው ወ/ሮ ሀቢባ አክለው ገልጸዋል።

ኢሬቻ ማለት ህብረ-ብሄራዊነት፣ ፍቅር፣ ሰላምና አብሮነት እንዲሁም ምስጋና የሚቀርብበት ነው ያሉት በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታሁን አበራ በክፍለ ከተማ ደረጃ በድምቀት እየተከበረ መሆኑንና በከተማ ደረጃ ለሚከበረው በአል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በአሉን ለማክበር ወደ ከተማ የሚመጡትን እንግዶች ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው ሁሉ ሁሉም የክ/ከተማው ነዋሪ አቀባበል እንዲያደርግ አቶ ጌታሁን መልእክት አስተላልፈዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.