
ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት! Irreecha : Olka'insa Biyyaaaf!
በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ/ም ኢሬቻ በዓል "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት!" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
የእለቱ የክብር እንግዳ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር ኢሬቻ የሰላምና የምስጋና በዓል በመሆኑ እህትማማችነትና ወንድማማችነት በማጠናከር በአብሮነትና በአንድነት በዓሉን ማክበር ይገባናል ብለዋል።
በዓሉን ስናከብር በእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ፣ በህዝቦች መካከል እህትማማችነትና ወንድማማችነትን የምናጠናክርበት እንዲሆን አሳስበዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው እንኳን ለ2018 ዓ.ም ለመላው ክፍለ ከተማው ነዋሪዎች የኢሬቻ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ያሉ ሲሆን ኢሬቻ በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር መቆየቱን አንስተዋል።
ኢሬቻ የምስጋና በአል ሲሆን፤ ከክረምት ወደ በጋ ስላሸጋገርከኝ አመሰግናለሁ በማለት ፈጣሪ የሚመሰገንበት የአብሮነትና የወንድማማችነት በአል መሆኑንም በመግለፅ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኤሬቻ ሲከበር ብዝሀ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ በሚያደርግና ባህላዊ ቱውፊቱን በመጠበቅ በሰላም፣ በአብሮነትና በወንድማማችነት መከባበርን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ጭምር በመሆኑ በዛሬው ዕለት በድምቀት አክብረነዋል ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው በመጨረሻም በአሉን በጋራ ስናከብር በሰፊ ሀገራዊ ሁለንተናዊ ለውጥ ውስጥ በመሆን በተግባር የሚታዩ ፕሮጀክቶች፣ህዝባዊ ተጠቃሚነትን የተረጋገጠበትና ድህነትን ተሻጋሪ ለአፍሪካ ሀገራት ዳግም ተምሳሌት የሆንበት ተግባራት ውስጥ ስንሆን ሁላችንም በመከባበር በወንድማማችነት በአሉን በጋራ በማሳለፍ አብሮነታችን አጠናክረን መሄድ ይገባል።
"ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድምና እህት ሕዝቦች ጋር በፍቅርና በአብሮነት የሚያከብረው በዓል ነው"
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ገነት ዋቅጋሪ በበኩላቸው የኦሮሞ ህዝብ በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የራሱ የሆነ ባህል እሴት እና ታሪክ ያለው ህዝብ ነው፡፡ የባህሉ እና እሴቱ ምንጭ የገዳ ስርዓት ነው፡፡
የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት ማሳያ የሆነውን የኢሬቻ በዓልን በዓመት 2 ጊዜ ያከብራል፡፡ እነሱም ኢሬቻ መልካ እና ኢሬቻ ቱሉ ናቸው፡፡ ኢሬቻ መልካ፡- ከጨለማው ክረምት ወደ ብርሃንማው ፀደይ ሲሽጋገር ከፈጣሪና ከፍጡር ጋር በመታረቅ ውስጥን በማፅዳት ለአለፈው ምስጋና የሚያቀርቡበት ለቀጣዩ ተስፋን የሚያድሱበት የምስጋና በዓል ነው፡፡ ኢሬቻ ቱሉ፡- በበልግ ወቅት ጤናማ የሆነ ዝናብ እንዲኖር ወደ ተራራ ወተው ፈጣሪን የሚለምኑበት በዓል ነው ብለዋል፡፡
የኢሬቻ በዓል አከባበር ስርዓትን ስንመለከት ከፖለቲካ፣ ከተለያዩ አምልኮዎች ነፃ የሆነ ጥላቻን የሚያርቅ ፍቅር፣ እርቅና አንድትን የሚያበረታታ ለብሄር ብሄረሰብ አንድነትና ለሀገር ግንባታ ትልቅ ሚና ያለው ስርዓት ነው በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.