ኢሬቻ የገዳ ስርዓት መገለጫ የአብሮነት፣ የሰላም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኢሬቻ የገዳ ስርዓት መገለጫ የአብሮነት፣ የሰላምና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነዉ! ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራዉ

"ኢሬቻ ለሀገር ማሰራራት!" በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በኒኮላ ሜዳ  የኢሬቻ ፌቲቫል አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣  የሀገር ሽማግሌዎች፣ የከተማና የክ/ከተማ አመራሮች፣ ፎሌዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ በተገኙበት ተከብሯል።

በፕሮግራሙ የተገኙት የአዲስ አበበ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሐይ ሽፈራው የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል የዘመናት ቁጭት የሆነው የህዳሴ ግድባችንን ባጠናቀቅነበት ማግስት መከበሩ ልዩ የሚያደርገው መሆኑን ገልፀው በዓሉ ባህሉንና ትውፊቱን በጠበቀ መንገድ በመከበር ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል::

የአዲስ አበበ ከተማ ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላና በበኩላቸው የኢሬቻ በዓል በመዲናችን አዲስ አበባ መከበሩ ለከተማችን የቱሪዝም ዘርፍ ተጨማሪ አቅም መሆኑን ጠቅሰው በዛሬው እለትም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የነበረው የኢሬቻ ፌስቲቫል በአይነቱ የተለየ ነበር ብለዋል::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው የኢሬቻ በዓል የአብሮነትና የፍቅር መገለጫ በመሆኑ በዓሉን በወንድማማችነት በአንድነት አክብረናል ሲሉ ገልፀዋል::

የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ በበኩላቸው የይቅርታና የምስጋና በዓል የሆነው ኢሬቻን እንዲህ ባማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ያደረጋችሁ በሙሉ ምስጋና ይገባቹአል ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.