
አዲስ አበባ ከተማ የኢሬቻ በዓልን ስታከብር የኢትዮጵያን ማህበራዊ መስተጋብር ለዓለም በሚያስተዋውቅ መልኩ መሆን እንደሚገባ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ
አዲስ አበባ ከተማ የኢሬቻ በዓልን ስታከብር የኢትዮጵያን ማህበራዊ መስተጋብር ለዓለም በሚያስተዋውቅ መልኩ መሆን እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል የዋዜማ ዝግጅት መርሃ ግብር ተካሂዷል።
አዲስ አበባ ከተማ በርካታ በዓላትን እሴታቸውን በጠበቀ ሁኔታ ስታከብር መቆየቷን የተናገሩት ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ መስከረም 24 በሆረ ፊንፍኔ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ለማክበር ወደ ከተማችን የሚገቡ እንግዶችን በተለመደው የእንግዳ አቀባበል ስሜት በመቀበል እና በማስተናገድ በዓሉን የኢትዮጵያዊያን ማህበራዊ መስተጋብራችንንና አንድነታችንን ለዓለም ማሳየት ይኖርብናል ብለዋል።
የሆረ ፊንፍኔ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ወደ ከተማው የሚመጡ እንግዶችን ተቀብለው ለማስተናገድ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎችም አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀቅ እየተጠባበቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.