ዛሬ የተመለከትናት ጂግጂጋ ባለፈው ጥር ከተመለከ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የተመለከትናት ጂግጂጋ ባለፈው ጥር ከተመለከትናት ይዞታዋ በሚታይ መልክ የተቀየረች ናት።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በመላው ከተማዋ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ሲሆን በኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በሁሉም አካባቢ የመኖሪያ ሁኔታን በግልጽ እያሻሻሉ ይታያሉ። የከተማ ማዕከሎቻችንን ስናዘምን የምንገነባው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገም መሠረት እያኖርን መሆኑን መገንዘብ ይገባናል። ርዕያችን እንደኢትዮጵያዊ እና አፍሪካዊ ጠቃሚ በሆኑልን ጉዳዮች ላይ የተተከለ መሆኑን ማስታወስ ይገባናል። 

በዚህ መንፈስ የሶማሌ ክልል በቱሪዝም አዳዲስ እድሎችን እየከፈተ ይገኛል። ወደመጠናቀቂያ ምዕራፍ በደረሰው የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ለምስራቁ የሀገራችን ክፍል አዲስ ዋጋ የጨመረ እድል እየፈጠረ ነው። በአጠቃላይም የተመለከትነው የሥራ እድገት በጂግጂጋ እና በመላው ክልሉ የሚስተዋለውን መነቃቃት የሚገልጽ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.