በመዲናችን አዲስ አበባ፥ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ጤናማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናችን አዲስ አበባ፥ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ጤናማ፣ ፅዱ፣ ውብ እና ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ዘርፈ ብዙ መሰረተ ልማቶች ተከናውነዋል፤ በመከናወን ላይም ይገኛሉ።

የኮሪደር ልማት፥ ከውበት ባሻገር!

የመንገድ ፣ አረንጓዴና የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች: አንፊዎችና ፕላዛዎች፣ የብስክሌት-መንገድ፣ የእግረኛ መንገድ፣ የህፃናት መጫወቻ፣ ተርሚናሎች እና  የመኪና ማቆሚያዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የህዝብ መፅዳጃ ቦታዎች እና የወንዝ ዳር ልማቶች ወዘተ...ተጠቃሽ ናቸው። 

ከመሰረተ ልማቱ ጎን-ለጎን ከ5000 በላይ ሱቆች እና ሞሎች ተሰርተው የከተማው ማህበረስብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል። ከ170 ሺ በላይ ሰዎች በግንባታ ሂደት የስራ ዕድል ተፈጥሮላችዋል። አሁንም በሁሉም አሚኒቲዎች በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በቀጥታ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል። 

በሌላ መልኩም፥ የተለያዩ የውጭና የውስጥ ኢንቨስተሮችን ያሳተፈ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመትንት ስራዎችም እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ለአብነትም በ2017 በጀት ዓመት  በግልና መንግስት የትብብር አጋርነት ስምምነት 1.56 ትሪሊዮን ብር  ካፒታል በጀት በመመደብ 4168 ባለሀብቶች ፈቃድ ያገኙበት ግዙፍ ኢንቨስትመንት እየተከናወነ ይገኛል። 

ሆኖም፥ የመዲናችን ከፍታ፣ የህዝቦቿን ምቾት፣ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ የማያስደስታቸው፣  የተሰራውን ልማት ለማጣጣልና ለማደናቀፍ  ሲሞክሩ ይታያል፡፡

ከራሳቸው ውጪ የሌላው ልማትና ዕድገት የሚያስከፋቸዉ  ከዚህም አልፎ በጀት የረዱን ይመስል ሊቆጣጠሩንና የሚበጀንን ሊወስኑልን ይዳዳቸዋል።

በርግጥ አዲስ አበባ በጀቷን ከብክነት በፀዳ በከፍተኛ ቁጠባ ስራ ላይ በማዋሏ የማንም እርዳታ እና ብድር ሳያስፈልጋት አለምን ያነጋገረ አስደናቂ ልማት አስመዝግባለች።አሁንም ወደፊት ለመረጠን ህዝብ በትጋትና በታማኝነት እያገለገልን፣  ለመኖር ተስማሚ ወብ እና ጽዱ እንደ ስሟ ዉብ አበባ የሆነች አዲስ አበባን መገንባታቻንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.