.png)
ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ ስኬታማነት!
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ/ም ኢሬቻ በዓል "ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ ስኬታማነት" በሚል መሪ ሀሳብ በሲንፓዝየም ተከብሯል።
የእለቱ የክብር እንግዳና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አብረሃም ታደሰ ኢሬቻ በዓለም በዩኒስኮ ከማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ ፣ በሀገራችን ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላቶች መካከል አንዱ መሆኑን ገልፀው ፣ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ከጨለማ ወደ ብረሃን ያሸጋገረውን ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ፣ የተጣላ የሚታረቅበት ፣ ቂም የሚረግፍበት በምትኩ አንድነት ፣ ፍቅር ፣ ሰላም ፣ እህትማማችነትና ወንድማማችነት የሚጠናከርበት ታላቅ የአደባባይ የህዝብ በዓል ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።
ክቡር አቶ አብርሃም አክለውም የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል ከሌላው ጊዜ ልዩ የሚያደርገው ሀገራችን ከተስፋ ብረሃን ወደ ሚጨበጥ ብረሃን የተሸጋገርንበት ፣ በከተማችን ከ19ሺ በላይ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የሆኑበት ፣ ከተማችን እንደስሟ ውብ አበባ አድርገን በተለይም ለበዓሉ ታዳሚዎች የበዓል ማክበሪያ ቦታ ደረጃውን የጠበቀና ምቹ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራበት ወቅት በመሆኑ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል በዓሉን ስናከብር በእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ፣ በህዝቦች መካከል እህትማማችነትና ወንድማማችነትን የምናጠናክርበት እንዲሆን አሳስበዋል
የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ጌታሁን አበራ ኢሬቻ ፍቅር ነው ፣ ኢሬቻ ሰላም ነው፣ ኢሬቻ በዓል በሚሊዮን የሚቆጠር የኦሮሞ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ፣ ከሌሎች ወንድምና እህቶቹ ጋር አንድነትን የሚጠናክርበት ትልቅ በዓል መሆኑ አስገንዝበው በሌላ በኩል የ2018ዓ/ም ኢሬቻ በዓልን ስናከብር ልዩ የሚያደርገው አትችሉም ሲሉን የነበሩትን አሳፍረን ችለን አሳይተናል በተግባር ገልጠን የኢትዮጵያን ማንሰራራት ያስመሰከርንበት መሆኑ ገልጿል።
አቶ ጌታሁን አክለውም አይቀሬ የሆነውን የኢትዮጵያ ብልፅግና ለማረጋገጥ ህዝባችንን አሰልፈን 7/24 እየሰራን የሀገራችን ማንሰራራት በተልዕኮ ውጤታማነት ብልፅግናችን እውን ማድረግ ይገባናል ብሏል።
ኢሬቻ ብዙ ህዝብ የሚያሰባስብ ፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የሚጠናክር ፣ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምተን እንድንኖር የሚያደርግ ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ትልቅ የአንድነት የአብሮነት የአደባባይ በዓል መሆኑን የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ስራ ክህሎት ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በላይነሽ ሞሲሳ ገልጿል።
የሲንቦዝየሙ ታዳሚዎችም የኢሬቻን ባህል በሚገልፁ በኦሮሞ የባህል አልባሳት አሸብርቀው ፣ የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎች ፣ ትርዕይቶችና ውዝዋዜዎችን ፈጠራዎችን ሲያሳዩ ቆይተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.