ኢሬቻ የሰላም የእርቅና የአብሮት መገለጫ በዓል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኢሬቻ የሰላም የእርቅና የአብሮት መገለጫ በዓል በመሆኑ ባህላዊ ወጉንና ትውፊቱን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተገለፀ ።

በዛሬው እለት "ኢሬቻ  ለሀገር ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማ ደረጃ የኢሬቻ በአልን ምክንያት በማድረግ  የማጠቃለያ የፓናል ውይይትና ፌስቲቫል  የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ  ከፍተኛ አመራሮች፣ አባ ገዳዎች፣ሀደ ሲንቄዎች፣ቀሬዎች፡ቄሮዎች፣ፎሌዎች፣ ፣ጥሪ የተደረገላቸው ነዋሪዎችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች  በተገኙበት ተከብሮ ውሏል።

የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ማሾ ኦላና የአዲስ አበባ ከተማ  ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ባስተላለፉት መልእክት የኢሬቻ በአልን ባለፉት አመታት  በዚህ መልኩ  በደመቀና ባማረ መልኩ  ስናከብር  በርካታ ድሎችን የተጎናፀፍንበት እንደነበር አስታዉቀዋል።

የዘንድሮ  የኢሬቻ በአል  እንደ ሀገር ብሎም እንደከተማ ከፍተኛ ድል ያስመዘገብንበት የህዝቦች ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት እንደሆኑ ያነሱት አቶ ማሾ የማንሰራራት እና የከፍታ ዘመን የደረስንበት የታላቁ ህዳሴ ግድብ በተጠናቀቀበት ወቅት በመሆኑ  በአሉ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል ባስተላለፉት መልእክት ኢሬቻ: የአንድነት ፣የወንድማማችነትና የእህታማማችነት ምልክት  የህብረ-ብሔራዊ አንድነትና ውበት መገለጫ ነው ሲሉ ገልፀው  ዕሴቱንም  ለቀጣዩ ትውልድ ተጠብቆ እንዲሄድ ማድረግ ይገባል ሲሊ ተናግረዋል።

በአሉ በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶዎችን በመቀበል  ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ገልፀዋል። 

የዘንድሮው የኢሬቻ  በዓል የኢትዮጵያን ብሔራዊ ኩራትና የጋራ ጥረት ፍሬ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ መመረቅ ጋር መገናኘቱ ትልቅ ትርጉም  አለው  ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ግድቡ የኢትዮጵያን የብልጽግና ተስፋና ብርሃን ያበሰረ እንደመሆኑ መጠን፣ ኢሬቻ ደግሞ ተስፋ፣ ፀጋ እና አዲስ ምዕራፍ መጀመርን የሚያመለክት ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

አቶ አሚ ሙሄ ዓሊ የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ እንደገለፁት ኢትዮጵያ የየራሳቸው እሴትና ትውፊት ያላቸው በርካታ አገር በቀል እምነቶችና ጥንታዊ ሀይማኖቶች ተቻችለው በአንድነት የሚኖሩባት የብዝሃነት ምድር መሆኗ የገለፁ ሲሆን በዚህም በዩኔስኮ  ከተመዘገቡ እና ኢትዮጵያ ለአለም ካበረከተቻቸው የማይዳሰሱ ከ15 በላይ ቅርሶች መካከል የገዳ ስርአት መገለጫ የሆነው ኢሬቻ የሰላም የእርቅና የአብሮት መገለጫ በዓል በመሆኑ ባህላዊ ወጉንና ትውፊቱን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ብለዋል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.