
" ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት " በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት መድረክ ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በሸገር ከተማ አስተዳደር መካከል መጪው የኢሬቻ በዓልን ምክያንት በማድረግ " ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት " በሚል ሀሳብ የፓናል ውይይት መድረክ አካሄዷል።
የሸገር ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ቱሉ የኦሮሞ ህዝብ ለተፈጥሮ ትልቅ ቦታ የሚሰጥና ቁርኝቱ የሰፋ ህዝብ መሆኑን በመጥቀስ የኢሬቻ በዓል ህዝቡ ብሩህ ቀን ያሳየውን ፈጣሪ የሚያመሰግንበት ትልቅ ትርጉም ያለው በዓል መሆኑንና የኢሬቻ በዓል የኢትዮጲያን ብቻ ሳይሆን የመላው አለም ህዝብ ድንቅ በዓል መሆኑን በማንሳት በዓሉ ሲከበር የእርስ በርስ ግንኙነትን በማጥበቅ ፣ አንድነትን ሰላምና ፍቅርን በሚሰብክና በሚያጠናክር እንዲሁም የሀገራችንን መልካም ገፅታ አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ሊከበር እንደሚገባ ጠቁመዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ የኢሬቻ በዓል ከገዳ ስርዓት ውስጥ የተገኘ የአብሮነትና ሰላምን ማብሰሪያ ፣ ከጨለማው ወደ ብርሀን በመውጣቱ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ፣ የመጪው ጊዜን ብሩህነት የሚበሰርበት ፣ አብሮ የመሻገር ፣ የአንድነት ፣ የሰላም ፣ የፍቅር በዓል መሆኑን በማንሳት የ2018 የኢሬቻ በዓል ልዩ የሚያደርገው የታላቁ ህዳሴ ግድብ በተመረቀ ማግስትና አዲስ አበባ ከተማ እንደ ስማዋ አዲስና ውብ በሆነችበት ወቅት የሚከበር መሆኑን በማንሳት በዓሉ በርካታ ሚሊዮን ህዝብ ወደ ከተማው በመግባት የሚያከብረውና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው በዓል በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዓሉ በሰላምና ዕሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በበኩላቸው የኢሬቻ በዓል በዩኔስኮ የተመዘገበው ገዳ ስርዓት አንዱ መገለጫ መሆኑንና የኢሬቻ በዓል በርካታ ህዝብና ቱሪስት ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚሳተፍበት ለፈጣሪ ምስጋናን የሚያቀርብበት ፣ ተለያይተው የቆዩ የሚገናኙበት ፣የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት መገለጫ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የደስታ ፣ የአንድነት አብሮ የማደግ ፣ የምርቃትና የብልፅግና በዓል መሆኑን በማንሳት የሸገር ከተማና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሰላሙን አስተማማኝ ማድረግ እንግዶችን ተቀብሎ በገዳ ስርዓት አስተናግዶ መሸኘት እንደሚገባ በማንሳት አስተዳደሩ የኢሬቻ በዓል ዕሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግድት ማድረጉን ገልፀዋል ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.