ዛሬ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአይነቱ የመጀመሪያ እና እጅግ ዘመናዊ የሆነዉን የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስን መርቀን ስራ አስጀምረናል ።

የከተማችን አስተዳደር በሚሰራቸዉ የልማት ስራዎች ሁሉ ኪነ ጥበብን አበይት የትኩረት አቅጣጫዉ አድርጎ እየተገበረ ይገኛል ።በዚህም ባለፉት ጥቂት አመታት ነባሮቹን በማደስ እና ዘመናዊ እና ደረጃቸዉን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ እንዲሁም አዳዲስ እና ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸዉ የቲያትርና የሲኒማ ኮምፕሌክሶች ገንብተን ለኪነ ጥበብ ዘርፉ እድገት አስተዋፆ እያበረከትን እንገኛለን ።

ዛሬ ያስመረቅነዉ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ  ፦ 
ባለ14 ወለል ህንፃ ፣2 ዘመናዊ ሲኒማ ቤቶችን 
፣የቲያትር አዳራሽ ፣ 3 የተለያዩ አዳራሾችን ፣ የሆቴል እና ሪስቶ ራት ዘመናዊ ካፍቴሪያዎችን እና  ፓርኪንግ አገልግሎት ይዟል ።

የጥበብ ስራ በአዳራሽ ብቻ የተወሰነ ባለመሆኑ እና ወደ ማህበረሰቡ ቀረብ እንዲል በከተማችን በተገበርነዉ ሁለንተናዊ ለዉጥ የተለያዩ የዉጭ የኪነ ጥበብ ስራ የሚከወንባቸዉ ከ 160 በላይ አንፊ ቲአትርና ፕላዛዎችን ገንብተን ለአገልግሎት አዉለናል ።

የኪነ ጥበብ ዘርፉ በፈጠረዉ ምቹ ሁኔታ የዉስጥ ቁጭትን በመፍጠር ትዉልድን በመልካም ስራ እንድናንፅ ከወዲሁ ጥሪዬን አቀርባለዉ ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.