.png)
የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳሚ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ኃይማኖት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የእምነቱ አባቶች፣ የኃይማኖቱ ተከታዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የታደሙበት እና በመስቀል አደባባይ የተከናወነው የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
የፀጥታ አካላት በዓሉ በሠላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግና የበዓሉ አከባባር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥምረት በመሰራቱ በስኬት ማክበር እንደተቻለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ከዚህ ቀደም ህዝብ በስፋት ወደ አደባባይ በመውጣት ያከበራቸው በዓላትና ኩነቶች በሠላም መከበራቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወሶ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም እያደረገ ላለው ቀና ትብብር እና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ መላው የፀጥታና ደህንነት ተቋማት አባላት እና አመራሮች የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በፀጥታና ደህንነት ተቋማት ስም ምስጋናውን እያቀረበ የህብረተሰቡ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.