.png)
የፍቅር፣ የሰላም፣ የወንድማማችነት እና የእትማማችነት መገለጫ የሆኑትን የመሰቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በድምቀት እና በሰላም ለማክበር በቅንጅት መስራት ይገባል! :- ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራው
የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓላት ሐይማኖታዊ ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ከአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር እና ከሸገር ከተማ አስተዳደር ከተውጣጡ ከ3ሺህ በላይ ከሚሆኑ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች የተሳተፉበት ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ ላይ የተገኙት ወ/ሮ አለምፀሐይ ሽፈራው በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የፍቅር፣ የሰላም፣ የአብሮነት፣ የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት መገለጫ የሆኑት የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በድምቀት እና በሰላም እንዲከበሩ የአዲስ አበባ ከተማ እና የሸገር ከተማ ወጣቶች በቅንጅት ልትሰሩ ይገባል ብለዋል።
የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በዩኒስኮ በማይዳሰሱ ቅርስነት የተመዘገቡ እና የኢትዮጵያን መለያ በመሆናቸው ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸው ጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፋ ወጣቶች ሚናችሁን ልትወጡ ይገባል ሲሉ ወ/ሮ አለምፀሀይ አሳስበዋል።
አዲሱ ዓመት የሁላችን አሻራ ያረፈበት ታላቁ ህዳሴ ግድብን አጠናቀን ያስመረቅንበትን ጨምሮ ትልልቅ ስኬቶች ያስመዘገብንበት ነው ያሉት ወ/ሮ አለምጸሐይ የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ ከፍ አድርጎ ለማስቀጠል በወንድማማችነት እና እህትማማችነት መንፈስ መስራት ይገባል ብለዋል
የሸገር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ቱሉ በበኩላቸው የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ አንድነትን የሚያጎሉ የአደባባይ በዓላት እንደሆኑ አውስተው የሁለቱ ከተሞች ትስስር በበዓል ብቻ የሚታጠር ሳይሆን በተጀመሩ የሰላም የልማት እና የብልጽግና ስራዎች በጋራ እየሰሩ ያሉት ስራ ሊጠናከር ይገባል ብለዋል።
የመሰቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ቅርጫፍ ፅ/ቤት የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ስዩም ከበደ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሰነዱ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችም የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን ከጋራ ማክበርን ጨምሮ በሌሎች በሌሎች የሰላም እና የልማት ስራዎች ላይ በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.