.png)
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከአጎራባች ሸገር ሲቲ መነ አቢቹ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ ነዋሪዎች ጋር በመጪው ቀናት የሚከበሩትን የመስቀልና የእሬቻ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ ህዝባዊ የውይይት መድረክ አካሄዷል።
በውይይቱ መድረኩ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ እንደገለፁት ከፊታችን የሚከበሩ የመስቀል ደመራና የእሬቻ በዓላት የፍቅር፣ የአብሮነታችን ማሳያዎችና የሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማጠንከሪያ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን በመሆናቸው በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ የአጎራባች የሸገር ሲቲ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች አበርክቷቸው የጎላ በመሆኑ በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሰብለ ታደሰ በበኩላቸው እንደገለፁት የመስቀል ደመራና የእሬቻ በዓላት በሰላም ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ከአጎራባች ሸገር ሲቲ ከተማ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀይማኖታዊ የጨዋነት ማሳያን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል ።
የየካ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና ባቀረቡት የማወያያ ሰነድ ላይ እንደተናገሩት በዓላቶቹ ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የሸገር ሲቲ ነዋሪዎች ከክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ጋር በመሆን በዓላቶቹ በሰላም ተከብረው እንዲውሉ የግንዛቤ ስራ በመስራት የአካባቢያችሁን ሰላምና ጸጥታ በማስከበር የድርሻችሁን መወጣት ይገባል ብለዋል።
የሸገር ሲቲ መና አብቹ ወረዳ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ግርማ ጉታ በበኩላቸው በአላቱ የጋራ ማንነት መገለጫዎች በመሆናቸው ሰላማቸው የተጠበቀ እንዲሆን የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ያሉ ሲሆን 2018 በጀት አመት ሰላም የሰፈነበትና የጋራ ሀገራዊ ውጤት የሚመዘገብበት እንዲሆን በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል ።
የውይይቱ ተሳታፊዎች የሆኑ ከኦሮሚያ ሸገር ሲቲ ክፍለ ከተማ የመጡ ነዋሪዎች ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በዋነኝነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት በዓላቶቹ ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ የበኩላችንን ኃላፊነት እንወጣለን ሲሉ ገልፀዋል ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.