የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የሸገር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የትስስር ሰነድ ፊርማ ተፈራረሙ።

ወ/ሮ ሊዲያ በማጠቃለያዉ እንደገለጹት፤ ለተግባር አፈጻጸም እቅድ ምሰሶ በመሆኑ የጋራ ተግባቦት ለመፍጠርና ለቀጣይ አፈጻጸማችን በርብርብ መስራትና የተሻለ ትስስር ተፈጥሮ በቀጣይም በግምገማዎች በመታገዝ ዉይይቱ ለላቀ አፈጻጸም አጋዥ ስለሚሆን በእቅዱ ላይ የተቀመጡ ጉዳዮችን ሳንሸራርፍ መዉሰድ ያስፈልጋል ብለዋል።

ተሳስረን በመስራታችን የመጡ ዉጤቶችን እንዳሉ ሆነዉ የመጡ ዉጤቶችን እየገመገምን መሄድ ያስፈልጋል ያሉት ሀላፊዋ ህዝቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ ላይ አፋችንን ሞልተን በድፍረት ልናወራ የምንችልበትን ስራ በሰላሙ ረገድ በርብርብ መስራት ያስፈልጋል በማለት ከፊታችን የሚከበሩ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ለይም በጋራ ተቀናጅቶ መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ባለፈው በጀት ዓመት በጋራ በመስራታችን የላቀ ውጤት ማስመዝገባቸውን እና የቀረበው የ2018ዓ.ም ዕቅድ የሁለቱም ከተሞች በጋራ የሚያሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣የሸገር ከተሞች ከዞኖችና ከአዲስ አበባ ከተማ በትስስር በመስራት በርካታ ህገወጥ ንግዶች፣የጦር ዝውውሮች እንዲሁም የፀረ ሽብሮችና ፅንፈኛ ሀይሎችን በጋራ ማክሸፍ እንደቻሉ አንዳንድ የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

የሸገር ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ቱሉ እንደተናገሩ፣ሁለቱም ከተሞች ለጋራ ዓላማ የሚሰሩ እና የፀጥታ ስራ ድንበርና ወሰን የሌለው በመሆኑ በጋራ በመስራታቸው ውጤታማ መሆናቸውንና፣በቀጣይም የሚከበሩ በዓላቶች ላይ የፀጥታ ስራ ላይ የቅድመ ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነም ገልጸዋል።

ሀላፊው አክለውም የህዝቡን ግንኘኝነቶችን በማጠናከር ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና ኃላፊነት ወስደው አከባቢያቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ እንዲሁም ዝርፊያ ንጥቂያና ወንጀል የሚፈጽሙትን ትኩረት ሰጥተን መከታተልና መስራት አለብን ብለዋል።

በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግና ቀጣይ በሚሰሩ የጋራ የፀጥታ ስራዎች ላይበሁለቱ አመራሮች አቅጣጫ ተሰጥቷል።

የሁለቱም ከተሞች ሰላምና ፀጥታ አስተዳደሮች የጋራ የቀጣይ በቅንኝት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ የትስስር ሰነድ በመፈራረምና በ2017 በጀት አመት የሸገር ከተማ ላበረከተው አስተዋፅዕ ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የእውቅናና ምስጋና ተበርክቶለት የዕለቱ የውይይት መድረክ ተጠናቋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.