.png)
የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸውን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር ሴቶች የበኩላቸውን አስተዋጽዖ መወጣት እንደሚገባቸው ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ "በእምርታና በማንሰራራት የታጀበ በዓላትን እናክብር "በሚል መሪ ቃል በመጪው ለቀናት የሚከበሩ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ከ11ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ ሴቶች ጋር ውይይት ተደረገ።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንደተናገሩት የመስቀል ደመራ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ እንዲሁም የኢሬቻ በዓል የኢትዮጵያዊነታችን አንዱ መገለጫ በመሆኑ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የዓለም በዓል ጭምር ስለሆነ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸውን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ሃላፊነቱን መወጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
በዓላቶቹ በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ ሴቶች ዋነኛ ባለቤቶች በመሆናቸውን የገለፁት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ አያይዘው የመስቀልና የኢሬቻ ስናከብር የራሳቸውን እሴቶችና ቱዉፊቶች ሳይለቁ እንዲከበሩ የራሳችንን አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባል በማለት ገልፀዋል።
የአደባባይ በአላትን ስናከብር የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን ሰላሙን ለማደፍረስ የሚሞክሩትን ተቀናጅተን በመስራት ያለምንም ኮሽታ በዓላዊና ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ለማስቻል የራሳችሁን ሀላፊነት መወጣት ይገባል ሲሉ ወ/ሮ ቆንጂት ገልፀዋል
የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ሀላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሰፋ ቶላ እንደተናገሩት የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላማም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የሴቶች ሚና ከፍተኛ ነው በማለት ገልፀዋል።
መስቀልና ኢሬቻ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበሩ አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግና ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር አንድነታችንንና አብሮነታችንን በሚያጠናክር መልኩ ማክበር እንደሚገባ የገለፁት አቶ አሰፋ ቶላ አያይዘው ሁለቱንም በዓላት በድምቀትና በሰላም ለማክበር ሴቶች ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው በማለት ገልፀዋል።
በዓላቶቹ በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ ሴቶች ዋነኛ ባለቤቶች በመሆናቸውን የገለፁት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ አያይዘው የመስቀልና የኢሬቻ ስናከብር የራሳቸውን እሴቶችና ቱዉፊቶች ሳይለቁና የኢትዮጵያብዝሃነት መገለጫ መሆኗን በሚያሳይ መልኩ እንዲከበር የራሳችንን አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባል በማለት ገልፀዋል።
የአደባባይ በአላትን ስናከብር የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን ሰላሙን ለማደፍረስ የሚሞክሩትን ተቀናጅተን በመስራት ያለምንም ኮሽታ በዓላዊና ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ለማስቻል የራሳችሁን ሀላፊነት መወጣት ይገባል ሲሉ ወ/ሮ ቆንጂት ገልፀዋል
የልደታ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ሀላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሰፋ ቶላ እንደተናገሩት የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላማም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የሴቶች ሚና ከፍተኛ ነው በማለት ገልፀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.