.png)
የኮልፌ ቀራኒዮ እና የሸገር ከተማ መልካ ፉሪና መልካ ኖኖ ክፍለ ከተሞች ነዋሪዎች ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቶቻቸውን በመጠበቅ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን በድምቀት ለማክበር እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገለፁ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከሸገር ከተማ አጎራባች ክፍለ ከተሞች ከሆኑት መልካ ፉሪና መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማዎች ጋር በመሆን ከፊታችን የሚከበሩ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት በድምቀትና ትውፊታቸው ተጠብቆ እንዲከበሩ የሚያስችል የህዝብ የውይይት መድረክ በዛሬው እለት ተካሔዷል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አሚ ሙሄ አሊ የመስቀልና የኢሬቻ በአላት በርካታ ህዝብ የሚታደምባቸው መሆኑን ገልፀው እነዚህ በአላት ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸው ተጠብቆ በሰላም እንዲከበሩ የክፍለ ከተሞቹ ነዋሪዎች መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።
አያይዘውም እነዚህ በአላቱ በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገቡ መሆናቸውን አስታውሰው መንግስት በድምቀት እንዲከበሩ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቀዋል።
በተለይም ወጣቶች ለፀጥታ አካላት ታዛዥና አጋዥ መሆን ፣የተከለከሉ ነገሮችን ባለመጠቀም የየራሳችንን ሚና መወጣት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።
የሸገር ሲቲ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ገለቱ ሁለቱም በአላት በርካታ ህዝቦች ወጥተው በአንድነት የሚያከብራቸው ሲሆኑ ባህላዊ ሀይማኖታዊ እሴቶቻቸው ተጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።
በአላቱ በርካታ ሰዎች በአንድነት የሚሰባሰቡበት ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑበት ህብረ ብሔራዊ አንድነት የሚያሳዩ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች በዓላቱ፣ የኢትዮጵያን እንግዳ ተቀባይነት እና አብሮነት በማሳየት ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቶቻቸውን በመጠበቅ የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን በድምቀት ለማክበር እየተዘጋጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.