
ዛሬ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ያስገነባናቸውን 1 ሺህ 671 ያህል ቤቶች ለአገር ባለውለታዎች ፣ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለከፋ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እና በወንዝ ዳርቻዎች ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አስረክበናል
የቤት ግንባታዎቹ አብሮነትን እና ጉርብትናን የሚያጠናክሩ፣ የህፃናት መጫዎችን ፣ የስፓርት ማዘዉተሪዎችን የያዙ፣ በአጠቃላይ ንፁህና ሰው ልጅ የሚገባውን የከበረ የአኗኗር ዘይቤ የሚያዳብሩ ናቸው።
ይህን በጎ ተግባር በእውቀታቸው፣ በሃብታቸው፣ በጉልበታቸው የደገፉ ልበ ቀና ባለሀብቶችን እና ያስተባበሩ አመራሮቻችንን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.