
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ዳዬ በንሳ የቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካን መርቀው ከፈቱ
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ዳዬ በንሳ የቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካን መርቀው ከፍተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ የልማት መሠረት እንደሆነ ያምናል፣ ለዚህም የተለያዩ ፖሊሲዎችን በማውጣት እና በመተግበር ዘርፉን እየደገፈ ይገኛል ብለዋል።
በቡና ምርት ላይ እሴት የሚጨምር ፋብሪካ በከተማችን በመመስረቱ ደስተኞች ነን፣ እንደ ከተማ አስተዳደርም ድርጅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገራችንን ቡና ለማስተዋወቅ እና ተወዳዳሪ ለመሆን በሚያደርገው ጥረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደረግም ገልጸዋል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸው፣ ክልሉ በዳዬ ደንሳ ቡና ላኪ ድርጅት እንቅስቃሴ ደስተኛ መሆኑን ገልጾ፣ በተሻለ ደረጃ የሀገራችንን ቡና እንዲያስተዋውቁ እና ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረግላቸዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገች ነው፤ ለመለወጧ የሚረዱ አገልግሎቶችም እየቀረቡ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የዳዬ በንሳ ቡና ላኪ ድርጅት አንዱ መስራች አቶ አሰፋ ዱካሞ፣ ድርጅቱ የቡና ምርት ላይ በስፋት እየሰራ እንዳለ ጠቅሰው፤ በ2017 ዓ.ም 8700 ቶን በላይ ቡና መላክ መቻሉን ገልጸዋ።
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ የተመረቀው ዘመናዊ የቡና ማቀነባበሪያ በ2 ቢሊየን ብር የተገነባ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ዳየ በንሳ ቡና በዘርፉ ለ20 ዓመታት የቆየ እና የኢትዮጵያን ቡና በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለውም ገልጸዋል።
ዳዬ በንሳ ወደ 30 የዓለም ሀገራት ቡናን እየላከ ያለ ድርጅት መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ዳየ በንሳ ቡና ላኪ ድርጅት 20ኛ የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለዲቦራ ፋውንዴሽን እና ለህብረት ለበጎ አድራጎት ማህበር ለዕያንዳንዳቸው የአንድ አንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.