.png)
"ዛሬ በ46 የተለያዩ የሞያ አይነቶች ስልጠናቸውን በውጤታማነት ያጠናቀቁ 7 ሺህ 149 የቴክኒክና ሞያ ሰልጣኞችን በታላቅ ድምቀት አስመርቀናል። ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
ባለፉት 2 ዓመታት በቴክኒክና ሞያ ስልጠና ዘርፍ ነባር ችግሮችን በመቅረፍ ለአገራዊ ብልፅግና የሚጠበቅበትን ጉልህ ሚና እንዲወጣ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአጭር ጊዜ አበረታች ውጤት እያስመዘገብን እንገኛለን። በተለይም በዘርፉ የሚሰጡ ስልጠናዎች የአገሪቱን የብልፅግና አቅጣጫ የተከተሉ እና የገበያው ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ማድረግ ችለናል።
ሰልጣኞች በቆይታቸዉ 70 በመቶ የተግባር እንዲሁም 30 በመቶ የንድፈ ሃሳብ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉ ክህሎትን በማላቅ፣ ፈጠራን በመጨመር አበረታች ውጤት እያመጣ ይገኛል።
ውድ ተመራቂዎች፤ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ ያለንበትን የውድድር ዓለም ከግምት በማስገባት ምንጊዜም ራሳችሁን በእውቀት፣ በክህሎት በተለይም በቴክኖሎጂ በማበልፀግ ፈጠራና ፍጥነትን የህይወታችሁ መርህ በማድረግ ስራ ፈጣሪ መሆን ይጠበቅባቹሀል። አስተዳደራችንም ይህን ለመደገፍ እንደ እስካሁኑ ሁሉ ከጎናችሁ መሆኑን ዳግም አረጋግጥላቹሀለሁ"።
መልካም የስራ ዘመን !
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.