
"ህዝብ ትልቁ ሀብታችን እና የስልጣን ባለቤት በመሆኑ ዝቅ ብለን ማገልገል፣ጆሮ ሰጥተን ማዳመጥና ቀርበን ጥያቄዎቻቸዉን መመለስ ከምክር ቤቱ የሚጠበቅ ቀዳሚ ተግባር ነዉ።"አፈጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር
አፈጉባዔዋ ይህን የተናገሩትት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ግብ ላይ የስምምነት ፊርማ ባከናወነበት ወቅት ነዉ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር በፊርማ ስነ-ስርዓት መርሀ ግብር ላይ በአደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደተናገሩት ባለፉት ዓመታት የጋራ ግብ አንግበን ብዙ እርቀት በመጓዝ ከተማችን የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን በርካታ ዉጤቶችን አስመዝግበን በዓለም የማንሰራራት አቅማችንን ማሳየት ችለናል ብለዋል፡፤
ለዚህም አንዱና ዋናዉ ታላቁ ህዳሴ ግድባችን መጠናቀቅ ዓለምን ያስደመመ ህያዉ የጋራ ታሪካችን ነዉ ያሉት አፈጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና "ህዝብ ትልቁ ሀብታችን እና የስልጣን ባለቤት በመሆኑ ዝቅ ብለን ማገልገል፣ጆሮ ሰጥተን ማዳመጥና ቀርበን ጥያቄዎቻቸዉን መመለስ ከምክር ቤቱ የሚጠበቅ ቀዳሚ ተግባር ነዉ ብለዋል፡፡
በዚህ አዲስ ዓመት ስንገናኝም ታላላቅ ስኬቶቻችንን በተግባር ጨብጠን ለቀጣይ የበለጠ ለመስራት የምንነሳሳበት ሀገራችን የሰነቀቻቸዉን ሌሎች አጓጊ ራዕዮች ወደ ተግባር ለዉጠን የብልፅግና ጉዛችንን እዉን የምናደርግበት ነወ በማለት አፈጉባዔዋ ገልፀዋል፡፡
አፈጉባዔዋ አክለዉም ይህ የዛሬዉ የፊርማ ስነ ስርዓት ከባለፈዉ ልምድ ወስደን በከተማችን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት፤ፍትሀዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ፤ሠዉ ተኮር ስራዎችን ለማጠናከር፤አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ጠንካራ ተቋም ለመገንባት ይበልጥ የከተማችንን ብልፅግና ሁለተናዊ በሆነ መልኩ ስኬታማነቱ እንዲረጋገጥ የጋራ ኃላፊነት የምንወስድበት ነዉ ብለዋል፡፡
በሚዲያና ኮሙኒኬሽን በኩልም የበለጠ የከተማዋን ገፅታ በመገንባት፣የወል ትርክትን በመትከል፤የህዝባችንን የመረጃ ፍላኀት ተደራሽ በማድረግ ፤የአጀንዳ ምንጭ እና ሰጪ በመሆን እንዲሁም የሳይበር ጥቃትን በመመከት የሀሰብ የበላይነትና የህዝባችን እርካታ የሚረጋገጥበት እንዲሆን እመኛለሁ በማለት አፈጉባዔ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር ለተገኙ ድሎች ምክር ቤቱን አመስግነዋል፡፤
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ፤ምክትል አፈ-ጉባዔ፤ቋሚ ኮሚቴዎችና የካቢኔ አባላት እና ከፍተኛ አመራሮች በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተዉ የስምምነት ፊርማቸዉን አከናዉነዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.