የገብያ ማረጋጋት እና የንግድ ቁጥጥር ግብረ ሀይ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የገብያ ማረጋጋት እና የንግድ ቁጥጥር ግብረ ሀይል በምርት አቅርቦትና በህግ ማስከበር ያሉ አፈፃፀሞች ና የ90 ቀናት እቅድ አፈፃፀም ተገመገመ::

የአዲስ አበባ አተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና የግብረ ሀይሉ ሠብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ መድረኩን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለዉ የግብረ ሃይል መዋቅር በተቀናጀ እና በተጠናከረ አግባብ በጥብቅ ዲሲፕሊን ተግባራትን በወጥነት እየገመገመ በመስራቱ በምርት አቅርቦት፤በህግ ማስከበርና መሰል ሰራዎች ላይ ስኬት ማስመዝገብ መቻሉ መሬት ላይ ያለ እዉነታ ነዉ ብለዋል፡፡

ለዚህም የግብይት ስርዓቱ ምቹ እንዲሆን ህገወጥ ነጋዴዎችንና ደላላዎችን መቆጣጠር የተቻለበት፤ በአንዳንድ ምርቶች ላይ እጥረት እንዳያጋጥም እና ገበያዉ እንዳይራብ የተሰሩ የቁጥጥር ስራዎች ዉጤታማ እንደነበሩ ጭምር ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩልም በመዲናችን በቀጣይ የሚከበሩ ትላልቅ ህዝባዊ በዓላት ያለምንም ስጋት እሴታቸዉን ጠብቀዉ እንዲከበሩ የበለጠ ትኩረት ሰጥተን በሙሉ አቅም ተረባርበን መስራት ይገባል ያሉት ኃላፊዉ በማህበራት፤በኢመደበኛ የግብይት ቦታዎች እና በሌሎችም የምርት እጥረት እና የዋጋ ንረት እንዳይኖር እንዲሁም ባዕድ ምርቶች ላይ ጥብቅ የክትትልና የቁጥጥር ስራ አጠናክሮ መሰራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

አያይዘዉም የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ ጥሩ ቢሆንም የደንብና የፀጥታ አካላት ወጥ በሆነ መልኩ ተቀናጅተዉ መስራትና ኃላፊነታቸዉን መወጣት  ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል፡፡

የገበያ ማዕከላትም ያለባቸዉን ችግሮች አቅም በፈቀደ ከወዲሁ በመፍታት በሙሉ አቅም እንዲሰራባቸዉ ጥረት ማድረግ ይገባል ያሉት አቶ ጃንጥራር ዓባይ የእሁድና የቅዳሜ ገበያ ስታንዳርዳቸዉን ለመስቀጠል እየተሰራ ያለዉን ስራ በማጠናከር ለበለጠ ዉጤታማነት ተቀናጅቶ መስራት ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የጎዳና ላይ ኤግዚቪሽንና ባዛር ግብይትን በሰፊዉ በማጠናከር የህብረተሰባችን የገበያ ፍላጎት በጠበቀ መልኩ ሃላፊነታቸዉን እንዲወጡ ለማስቻል ተገቢዉን ድጋፍና ክትትል ማድረግ የገባል ብለዋል።

በአጠቃላይ የምርት አቅርቦትን በማስፋት፤ተመጣጣኝና ፍትሃዊ የዋጋ የግብይት ስርዓት በማስፈን የሃገር ሃብት የሆኑትን የመስቀልና የእሬቻ በዓላት እሴታቸዉን አስጠብቀን በማክበር የህዝብ ትስስርን ይበልጥ ማስቀጠል ከሁላችንም የጠበቃል በማለት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.