.png)
"ኢትዮጵያ ችላለች" በሚል መሪ ቃል የታላቁ ህዳሴ ግድብ የ14 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬም መጎብኘቱ ቀጥሏል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁን የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ አስመልክቶ በከተማ ደረጃ ያዘጋጀዉ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ ዛሬም ቀጥሎ የመዲናችን የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እየጎበኙ ናቸዉ።
እንደጥንት አባቶች እና እናቶች በደምና በአጥንት ያቆየናት ሃገር ዛሬም በልጆቿ ደምና ላብ "ዓባይ" ጠብታዉ ሳይቀር ባለቤት መሆኗን በማየታችን ለእኛ ለኢትዮጵያዉያን ድርብ ድል በመሆኑ ኩራት ተሰምቶናል በማለት ጎብኚዎቹ ገልፀዋል፡፡
ጎብኚዎቹ አክለዉም የዉሃ ሃብታችንን በራሳችን እራሳችን ተጠቅመን ሌሎችም እንዲጠቀሙ ማድረግ መቻላችን ሃገራችን የነበራት አብሮ የማደግና የመበልፀግ ታሪኳ ዳግም የተበሰረበት ከደስታ በላይ የሚገለፅ አኩሪ የማንነት ህያዉ መገለጫችን ነዉ ብለዋል፡፡
የሃገርና የህዝብ እድገት ቀጣይነት የሚኖረዉ በትዉልድ መካከል ያለዉን ቅብብሎሽ በማያቋርጥ ሂደት ማስቀጠል በመሆኑ ወጣቱ ትዉልድ ከስኬቶቻችን በመማር ኢትዮጵያ ገና ብዙ መስራት እንደምትችል ማሳየት እንደሚገባዉ ገልፀዋል፡፤
ይህ ጅምራችን በመሆኑ ለሃገርና ለህዝብ የሚበጁ ሌሎች ታሪኮችን በመስራት ሀገራችንን በከፍታ ማማ ላይ ማፅናት ወጣቱ ይጠበቅበታል ሲሉም አስተያታቸዉን ሰጥተዋል፡:
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.