.png)
"ኢትዮጵያ ችላለች" በሚል መሪ ቃል የታላቁን ህዳሴ ግድብ የ14 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተጎበኘ ይገኛል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁን የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ አስመልክቶ በከተማ ደረጃ ያዘጋጀዉ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ ከተለያዮ የማህበረሰብ ክፍል የተዉጣጡ ነዋሪዎች እየጎበኙ ።
በአዉደ ርዕዩ ጎብኚዎች እንደገለፁት በመሪዎቻችን ቁርጠኝነትና በህዝባችን ሁለገብ ተሳትፎ በዚህ ትዉልድ ህያዉ የሆነ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትሩፋት ያለዉ የልማት ስራ በስኬት ተጠናቆ ማየታችን በዘመናችን ያየነዉ ሌላዉ ታላቅ ድላችን ነዉ ብለዋል።
አክለዉም ይህ ትዉልድ ከዚህ ህያዉ የሆነ ስራ በተጨማሪ ሌሎች ለሀገርና ለህዝብ የሚጠቅሙ የላቁ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበት ገልፀዉ እዉነትም ኢትዮጵያ የምትችል ሳይሆን ችላ የተገኘች፤በዓለም አደባባይ ጎልታ የታየች ሉዓላዊት ሀገር መሆኗን ተናግረዋል።
አዉደ ርዕዩ በሌሎች የከተማዋ የማህበረሰብ ክፍሎች እንደሚጎበኝም ታዉቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.