.png)
ምስጋና ብሔራዊ ድሉን ላከበረዉ ፣ ብሔራዊ ጀግኖቹን ላመሰገነዉ የከተማችን ነዋሪ በሙሉ !
ዛሬ ማለዳ በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜትና ድል አድራጊነት በነቂስ ወደ አደባባይ በመትመም ደስታዉን ለገለፀዉ ብሔራዊ ጀግኖቹን ላመሰገነዉ መላዉ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለዉ !
ክቡር ፕሬዚዳንት ታዬ አዝቀስላሴ ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ የዲፕሎማሲዉ ማህበረሰብ በተገኙበት መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች ከመቀነቱ ፈቶ ፣ ካለዉ ቆርሶ ፣ የኑዛዜዉ አካል አድርጎ ፣ ህፃናት ተማሪዎች ሳይቀሩ የከረሜላ መግዣቸዉን ለቦንድ መግዣ አዉለዉ፣ ብዙ አለም አቀፍ ጫና ዉስጥ በደምና አጥንት መስዋትነት ገንብተዉ ለፍፃሜ ያበቁትን የህዳሴ ግድብ ድል በታላቅ ድምቀት አክብረዋል ።
መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች የሌሊት ቁር የዛሬዉ ከባድ ዶፍ ዝናብ ሳይበግራችሁ የዘመናት ፣የትዉልዶች ትግል ዉጤት የሆነዉ ድላችሁን በጋራ አክብራቹሃል ፣ ለዚህ ድል ከነበራችሁ ደጀንነት አንፃር ይገባቹሀል !
ይህ ድል የኢትዮዽያ የመቻል ማሳያ ፣የአይቀሬዉ ብልፅግናችን ማረጋገጫ ብሔራዊ ምልክት ነዉ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን !
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.