የህዳሴ ግድብ ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የህዳሴ ግድብ ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ታላቅ ገድል ነው :: ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

የህዳሴ ግድቡ ትናንት የነበረውን የኢትዮጵያ የመንፈስ ጥንካሬ የሚያረጋግጥ፣ ዛሬ ያለንን ጥበብ እና ብልሃት የሚቃኝ ፣ ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ታላቅ ገድል ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናግረዋል፡፡

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ መመረቁን ተከትሎ ''ኢትዮጵያ ችላለች'' በሚል መሪ ቃል  በአዲስ አበባ ከፍተኛ ሕዝባዊ የድጋፍ እና የምስጋና ሰልፍ ተካሂዷል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የህዳሴ ግድብ ሃሳባዊ ሃይሉ ብርቱ፤ መልእክቱም እንችላለን ነው ብለዋል፡፡

የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን የመንፈስ ጥንካሬ የሚያረጋግጥ፣ ዛሬ ያለንን ጥበብ እና ብልሃት የሚቃኝ ፣ ነገ የሚኖረንን የብርሃን ቀንዲል የሚያሳይ ታላቅ ገድል ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

#ኢትዮጵያ ችላለች #GERD #Ethiopia #addisababa


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.