
ዛሬ በተካሄደው የድጋፍና ምሰጋና ህዝባዊ ሰልፍ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ካስተላለፉት መለዕክቶች፡-
👉የህዳሴው ግድብ ከህፃን እስከ አዋቂ በአንድ ድምጽ ፤ በአንድ ቁመና በህብረ ብሄራዊነት የገነባነው የላባችን፤ የደማችን የአይበገሬነታችን እውነተኛ ትዕምርት/ምልክት/ ነው፡፡
👉ታላቁ የህዳሴ ግድብ የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ድል ፤
👉ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፈታኝ በሆነው ሃሩር፣ በልበ ሙለነት፣ ለታላቁ ብስራት በጽናት ሙያቸዉን፤ ላባቸዉን ፤ እዉቀታቸዉን መስዋት ባደረጉ ጀግኖች የታነጸ የታሪክ መሰረት ፣
👉ታላቁ የህዳሴ ግድብ የዲፕሎማሲ፤ በጥብቅ የአገር ፍቅር ፤ ሙያዊ ስነ -ምግባር፤ አርበኝነት፤ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ትጋት ውጤት ፣
👉የህዳሴ ግድባችን የጂኦ ፖለቲካን ብያኔን የለወጠ ፤ የዲፕሎማሲን የተንሸዋረረ ተፅዕኖ የቀየረ ፣
👉የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለመላው ጥቁር ህዝቦች የማንሰራራት ድልን ያበሰረ፤
👉ታላቁ የህዳሴ ግድብ የአይበገሬነት ተምሳሌት የአንድነታችን እና የጋራ አሸናፊነታችን ዘላለማዊ ሃውልት፤
👉የታላቁ ህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ልጆች ከሃሳብ አመንጪነት እስከ ፈፃሚነት፤በላብ፤ በደምና አጥንት የተገነባ የሉአላዊነታችን መሰረት ፣
👉ይህ ትውልድ ! ታሪክ ዘካሪ ብቻ ሳይሆን እንደ ቀደምቶቻችን ታሪክ ሰሪ ጭምር ነው፤
👉በህዳሴው ግድብ ያስመዘገብነው ድል በጊዜ ወይም ደግሞ በደቂቃዎችና በሰዓታት ውስንነት የሚወሰን ድል አይደለም ፤ ይልቁኑ ትውልድን ሚሻገር ነው፣
👉የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድል ከድህነት የመዉጣት በራስ አቅም ለመልማት የመሻት፣ የቁጭት፤ የፅናት ዉጤት ነዉ፣
👉ሰማይ አገሬ፣ ምድር ወንበሬ እንደሚባለው ሁሉ በራስ ምድር፣ በራስ አቅም የመስራትን አቅም የገነባን በመሆኑ ትጋታችንን አጠናክረን የምንቀጥልም ይሆናል ፣
👉ይህ ግድብ እንደ አድዋ ሁሉ በአለም ፊት ፅናታችንን እና አንድነታችንን ያሳየንበት የወል ድላችን ነዉ ፤
👉የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድል ከተባበርን እና በአንድነት ከቆምን የትኛውም ምድራዊ ሃይል ከውጥናችን እንደማያቆመን ዳግም የተማርንበት ነው ፡፡
#ኢትዮጵያ ችላለች #GERD #Ethiopia #addisababa
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.