“ለኢትዮጵያ የብሩህ ተስፋ ቀንዲል ለሆነው የሕዳ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ለኢትዮጵያ የብሩህ ተስፋ ቀንዲል ለሆነው የሕዳሴ ግድብ በድል መጠናቀቅ እንኳን አደረሳችሁ” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ መመረቁን አስመልክቶ “ኢትዮጵያ ችላለች!” በሚል መሪ በአዲስ አበባ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል። 
 
በድጋፍ ሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ “ለኢትዮጵያ የብሩህ ተስፋ ቀንዲል፣ የታሪካችን እውነተኛ እጥፋት፣ የማንሰራራት ድንቅ መሠረት ለሆነው ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ታሪካዊ እና ሕዝባዊ ድል እንኳን አደረሰን፣ እንኳን አደረሳችሁ! ሲሉ የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል። 
 
የአዲስ አበባ ሕዝብ ከሕፃን እስከ አዋቂ፣ ከደሃ እስከ ሀብታም፣ ከተማሪ እስከ ምሁር፣ ከሕዝብ እስከ መሪ በአንድ ድምፅ፣ በአንድ አቋም፣ በኅብረብሔራዊ አንድነት በደማቁ ለተጻፈው እና ለማይደበዝዘው ደማቅ አሻራ መቀነታችንን እና ቀበቶአችንን አጥብቀን ከእለት ጉርሳችን በላባችን፣ በደማችን ጭምር የገነባነው የወል ስኬታችን፣ የድል ብስራታችን ለሆነው ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በአብሮነት ደስታችንን ለመግለጽ እና ለጀግናው እና ለማይበገረው ሕዝባችን ምስጋና ለማቅረብ በመስቀል አደባባይ ተገናኝተናል ብለዋል።  
#ኢትዮጵያ ችላለች 
#GERD #Ethiopia #addisababa 
 
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.