
ዛሬ የታላቁ ህዳሴ ግድባችን የ14 ዓመት ጉዞ፤ በተለይም የህዝቡን ተሳትፎ የሚያሳይ የፎቶ፣ የስዕል እና በአባይ ዙሪያ የተፃፉ መፃህፍት አውደ ርዕይ እና ፓናል ውይይት አካሂደናል።
ኢትዮጵያ ችላለች !
በፖናል ውይይቱ የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ያለዉ ፋይዳ፣ ከጂኦስትራቴጂካዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና መሸጋገር፣ የህዝብ አንድነትና ተሳትፎ ትርጉም አስመልክቶ በምሁራን ትንታኔ ቀርቧል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት 14 ዓመታት ያለፈበት ውጣ ውረድ፣ የተገኙ ድሎች፣ የውሃ ፖለቲካ ምንነት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ጽሁፎች ቀርበው ወይይት ተካሂዷል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.