.png)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁን የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ምክንያት በማድረግ በከተማ ደረጃ የፓናል ውይይት አካሔደ
በፓናል ዉይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር የአደረጉት የአዲስ አአባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ እንደገለፁት ለዘመናት ስናለቅስበት እና ስንቆጭበት የነበረዉ ዓባይ መቋጫ አግኝቶ እምባችን ጉባ ላይ ታስሮ ንጋት ሀይቅ ፈጥረናል ብለዋል።
ዓባይ ከሀይል ባለፈ በዲፕሎማሲዉ እኛ ኢትዮጽያዉያኖች ከፍ ብለን የአፍሪካ ዉኪሎች ጭምር መሆን የቻልንበት በደምና በላብ የታጠረ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።
አክለዉም ስትተባበር እና በጋራ ስንተም የማናሳካዉ ምንም ነገር እንደማይኖር የመጣንባቸዉ የስኬት ጉዞዎችና የዓባይ ድል ማሳያዎቻችን ናቸዉም ብለዋል።
ከመሪያችን ጀምሮ የታየዉ እምባ በአንድ ቋት ዉስጥ ያለ የኢትዮጵያን ህዝብ እምባ ፣የዘመናት ቁጭት በዉጤት የታጀበበት፣የደስታ ምንጭ፣የሀገር ብልፅግና መዳረሻ አመላካች መሆኑን ገልፀዋል።
ዉይይቱ በቀጣይ ለምንሰራቸዉ ስራዎች የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ መልካም አጋጣሚ በመሆኑ ልንጠቀምበት የሚገባ ነዉ በማለት ለተገኙት የጋራ ድሎች ህዝባቸዉንና መንግስታቸዉን በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.