
የኢፌዴሪ የገቢዎች ሚኒስቴር የ2018 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በቦሌ ክፍለ ከተማ ለተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተጠቃሚዎች ማእድ አጋርተዋል::
በተስፋ ብርሃን ቁጥር 26 የምገባ ማዕከል በተካሄደው የምሳ ግብዣ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ባደረጉት ንግግር የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ወገኖችን በቀን አንድ ጊዜ የተሟላ የምገባ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን የተናገሩት ሚኒስትሯ፣ የገቢዎች ሚኒስቴርም በዚህ የተቀደሰ ተግባር በመሳተፍ የድርሻውን አስተዋጽኦ በማበርከቱ ከፍተኛ ደስታ እንደሚሰማው ገልጸዋል፡፡ “
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖች በምግብ አቅርቦት ተጠቃሚ እንዲሆኑ 26 የምገባ ማዕከላትን ከፍቶ ለአገልግሎት ማብቃቱን አውስተው፣ በዚህ ተግባር የተለያዩ ተቋማት ተባባሪ በመሆን ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በልዩ ልዩ መስኮች ከተገኙት ስኬቶች ጎን ለጎን በሰው ተኮር ሥራዎች የበርካቶችን ሕይወት ለመለወጥ መቻሉን የተናገሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙት ሁለት የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በርካታ ወገኖች ተጠቃሚ መሆናቸውን በመግለጽ ይህ እንዲሳካ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.