ያሳለፍነው ዓመት ድርብ ድል ያስመዘገብንበት ፣...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ያሳለፍነው ዓመት ድርብ ድል ያስመዘገብንበት ፣ ለቀጣዩ ዓመት ስንቅ የሚሆን እና የጀመርነውን ሁለተናዊ ብልፅግና ከዳር ለማድረስ ዳግም ቃል የምናድስበት ነው ሲሉ ወ/ሮ አለምፀሃይ ሽፈራው ገለፁ ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ  በሚገኘው 21ኛው ተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል በረከት ገበሬዋ ቅርንጫፍ  የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር  ቢሮ ፣የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን  ከክፍለ ከተማው አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን የ2018  አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ  ለአቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ወገኖች የማዕድ ማጋራት  መርሀ-ግብር አካሂደዋል ።

በማዕድ ማጋራቱ የተገኙት  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራው ባለፉት ዓመታት  ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር  መሆኑን ያረጋገጠበት  እንደነበር አስታውሰው የዘንድሮን አዲስ ዓመት ድርብ ድል ያስመዘገብንበት ለቀጣዩ ዓመት ስንቅ የሚሆን እና የጀመርነውን ሁለተናዊ ብልፅግና ከዳር ለማድረስ ዳግም ቃል የምናድስበት ነው ሲሉ ተናግረዋል ። 

አዲሱ ዓመት  የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለምረቃ የበቃበት  መሆኑን ያወሱት ወይዘሮ አለምፀሃይ   ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ የዕድገት ምዕራፍ እየተሸጋገረች መሆኗን ያበሰረ እንደሆነም ተናግረዋል።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ  ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል  ማዕድ በማጋራት የቆየው ኢትዮጵያዊ ባህል እና እሴቶችን  በመጠበቅ አብሮነትን እና መደጋገፍን በማጠናከር የገባል ያሉ ሲሆን ክፍለ ከተማው  በምገባ ማዕከሉ የሀገር ባለውለታወቻችን እና  በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎቻችንን ማዕድ በማጋራት በዓልን በአብሮነት ማሳለፉን ገልፀው  ሰው ተኮር ተግባራት ከበዓል ባሻገርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል  ተናግረዋል  ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.