
እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን
በ2017 በርካታ ስኬቶች አግኝተን፣ የኢትዮጵያ መጪ ብሩህ ዘመን ገላጭ የሆነውን ታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ በማስመረቅ ወደ 2018 ዓ.ም በድል ታጅበን እየተሻገርን ነው።
አዲሱ የ2018 ዓመት የእቅዶቻችንን ፍሬዎችን የምናይበት፣ አዳዲስ መልካም የተግባር ዘሮችን የምንዘራበት፤ በትጋት እና በቁርጠኝነት ለሕዝባችን የገባነውን ቃል የምንፈጽምበት አመት እንዲሆን እመኛለሁ!!
መላው ኢትዮዽያዊያን ፣የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃትና ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ !!
መልካም አዲስ ዓመት
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታ እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.