
በአዲስ አመት ለከተማችን ነዋሪዎች እነሆ ገፀ በረከት “አዲስ-መሶብ”!
የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ እንዲሆን በቁርጠኝነት መስራታችንን ቀጥለናል::
ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተገኙበት "አዲስ መሶብ "የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ አስጀምረን በአዲሱ አመት ዋዜማ እነሆ ገፀ በረከት ብለናል።
በአስራ ሶስት ተቋማት ፤ መቶ ሰባት አገልግሎቶችን የሚሰጠው አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል የነዋዎቻችን እንግልት የሚቀንስ ፣ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት አዲስ ብስራት ይዘን መጥተናል።
በአዲሱ አመት በብዙ ብርታት እና ትጋት ልናገለግላችሁ ቆመናል ።
መልካም አዲስ አመት !
ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.