የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ከአለም ባንክ ሲንየር ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ኤግዚል ቫን ትራትስንበርግ ጋር የቃሊቲን የውሃና ፍሳሽ ማጣሪያ ማእከል ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱም በአለም ባንክ ይሁን በየትኛውም የብድር አቅርቦት የሚሰሩ ፕሮጀከቶች በተያዘላቸው ጊዜ የማጠናቀቅ ልምድ ከተማ አስተዳደሩ እያሳደገ መምጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ክንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ  ገልጸዋል፡፡  

በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ባህል እየሆነ መጥቷል ያሉት አቶ ጃንጥራር  የቃሊቲ የውሃና ፍሳሽ ማጣሪያም አንዱ ማሳያ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ 

ከተማው ከ70 ፐርሰንት በላይ የሚሆነውን በጀት ለካፒታል ፕሮጀክቶች እንዲውል እያደረገ ሲሆን ከፕሮጀክቶቹ መካከልም የውሀ እና ፍሳሽ ማጣሪያ ልማት ሰራ ግንባር ቀደም በጀት ከሚያዝላቸው ተቋማት ተጠቃሽ መሆኑን አብራርተዋል። 

ከተማ አስተዳደሩ ከቃልቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ በተጨማሪ  የፍሳሽ አወጋገድን ለማዘመን ኮሪደር የሚለማባቸውን አካባቢዎች ጨምሮ በሌሎችም ጣቢያዎች ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያዎችን ሰፊ በጀት መድቦ እየገነባ  እንደሆነ አቶ ጃንጥራር  ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም አዲስ አበባ ከተማ ካላት የውሃ ፍላጎት አንጻር ላለፉት ሶስትና አራት አመታት ሰፊ ስራ ቢሰራም አቅርቦቱን በስታንዳርድና ፍላጎትን ታሳቢ ባደረገ ሁኔታ ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ ገልጸው የንፁህ ውሃ ፕሮጀክቶችን ለመስራት ከአለም ባንክ እና ከሌሎች ትላልቅ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ አቶ ጃንጥራር  አብራርተዋል::

የመዲናዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፕሮጀክት የመተግበር አቅም የገነባ ተቋም በመሆኑ ከተቋሙ ጋር አብሮ መስራት አዋጭ መሆኑንም ጠቁመዋል::

አቶ ጃንጥራር አያይዘውም ከተማ አስተዳደሩ ብድር ከመመለስ አኳያም የሚጠበቅበትን እየፈፀመ ያለ መሆኑ አብሮ ለመስራት ምቹ የሆነ ከተማ እንደሆነ ገልፀዋል::

የአለም ባንክ ሲነር ማኔጅንግ ዳይሬክተርን ፕሮጀክቱን በመጎብኘታቸው አመስግነው አብሮ ለመስራት ከተማ አስተዳደሩ ዝግጁ ንውም ብለዋል።

የአለም ባንክ ሲንየር ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ኤግዚል ቫን ተራትስንበርግ በበኩላቸው አዲስ አበባ ከተማ  የሚያካሂደውን የፕሮጀክት አፈጻጸም አድንቀው በቀጣይም  ከከተማ አስተዳደሩ ጋር አብረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.