ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ስለ ታላቁ የኢትዮጵ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምን አሉ👇👇👇

የኢትዮጵያውያን ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ ለምረቃ መብቃቱ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል፡፡

ሁነቱን ከዘገቡት መገናኛ ብዙሃን መካከል ቢቢሲ፣ ሮይተርስ፣ አሶሺየትድ ፕሬስ፣ አልጀዚራ፣ ፍራንስ-24፣ ዴይሊ ኔሽንን ይጠቀሳሉ፡፡

👉ቢቢሲ "የኢትዮጵያውያን ኩራት" ሲል የገለጸው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በይፋ መመረቁን ዘግቧል፡፡

👉ፍራንስ-24 "ኢትዮጵያ ሚሊዮኖችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደርገውን ግዙፍ ግድብ ገንብታ አጠናቀቀች" ሲል ዘግቧል፡፡

"ኢትዮጵያ ለሚሊዮኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ማዳረስ የሚያስችላትን በአፍሪካ ግዙፍ የሆነ የኃይል ማመንጫ ግድብ መረቀች" ሲል የዘገበው ደግሞ ሮይተርስ ነው፡፡

👉አሶሺየትድ ፕሬስ በበኩሉ "ኢትዮጵያውያን ተስፋን የሰነቁበት በአፍሪካ ግዙፍ ግድብ ተገንብቶ ተጠናቀቀ" ሲል አስነብቧል፡፡

👉ዴይሊ ኔሽን የግድቡን መመረቅ በተመለከተ ባወጣው ዘገባ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት ስጦታ ሲል ገልጾታል፡፡

ዴይሊ ኔሽን የግድቡን መመረቅ በተመለከተ ባወጣው ዘገባ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ "የኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት ስጦታ" ሲል ገልጾታል፡፡

👉በተመሳሳይ አልጄዚራ፣ ሲኤንቢሲ አፍሪካ፣ የቱርኩ አናዶሉ ኤጀንሲን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ምረቃ ዘግበዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.