.png)
የክረምት ወራት ስንብትና የፀደይ መምጣትን የሚያበስሩበት የጎቤ” እና “ሽኖዬ” ባህላዊ ጨዋታዎች በአድዋ መታሰቢያ ተከበሩ።
በዓላቱ በወንዝ መሙላት ተቋረጦ የቆየው የቤተ ዘመድ መጠያየቅ እና ማኅበራዊ ግንኙነት የሚጀምርበት የብሩህ ወራት ጅማሮ ሆነዉ ይከበራሉ፡፡
ጎቤ እና ሽኖዬ ባሕላዊ የወጣቶች ጨዋታዎች በገዳ ሥርዓት የባሕላዊ እሴቶች ውስጥ ይካተታሉ።
በዚህ ወቅት ቤት ለቤት በመዘዋወርም “ለምለም ሳር ” እየሰጡ መልካም ምኞታቸውን ይገልጻሉ::
የበርካታ ባህሎች እና ትውፊቶች ባለቤት የሆነችው ሃገራችን ኢትዮጵያ ያሏትን የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቿ ወደ አደባባይ በማውጣት የቱሪዝም ዘርፉን ማሳደግ ይገባል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.