ዛሬ በከተማችን ያስገነባናቸውን የገበያ ማዕከላት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በከተማችን ያስገነባናቸውን የገበያ ማዕከላት፣ የመኪና ማቆሚያዎች እና ተርሚናሎች ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።

አዲስ አበባ እንደ ስሟ እያበበች ለነዋሪዎቿ ምቹ ለጐብኚዎቿ ሳቢ ሆናለች።
በቀድምዋ አዲስ አበባ ይከናወኑ የነበሩ በጣት የሚቆጠሩ አለም አቀፍ ኩነቶች በመጡ ቁጥር የከተማዋን የተጎሳቆሉ ገፅታዎች ፣ የተበከሉ አካባቢዎች ፣ አንገት አስደፊ ገፅታዎች በጥቅሉ ገመናችንን ሌሎች እንዳያዩት በረጃጅም ባነር የመሸፈን ታሪክ በልጆቿ የሌት ተቀን ትጋትና በነዋሪዎቿ ትብብር ታሪክ ሆኗል ።

ዛሬ ከማለዳዉ አንስቶ ከአራዳ ጀምረን፣ በሜክሲኮ ፣ በለገሀር እና ሳር ቤት የአፍሪካ ህብረት አካባቢ የከተማችንን ገፅታ ይበልጥ የሚያሻሽሉ ፣ ለወጣቶችና ሴቶች ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ፣ የትራፊክ ፍሰቱን እያሳለጡ ፣ የሚያዘምኑ  የአካባቢዎቹን ዉበት የሚጨምሩ ፕሮጀክቶችን ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።

ለአብነትም አራዳ( ባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ) እና ፓርኪንግን እንዲሁም  አፍሪካ ህብረት  ጋር ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ፣ ፓርኪንግና  የህፃናት መዝናኛ ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ።

የአፍሪካ ህብረት  የገበያ ማዕከልና ፓርኪንግ የተሰራዉ ለዲፕሎማሲዉ ማህበረሰብ የተለያዩ የስጦታና የባህል መሸጫዎችን በአቅራቢያዉ እንዲያገኝ የሚያስችል ሲሆን በ28,500 m2 ላይ የተገነባ ዘመናዊ ማዕከል ነዉ፣ሁለት ቤዝመንትና ፕላዛ  ፣ 250 ሱቆች እና 250 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ይችላል ፣ በተጨማሪም የህጻናት መጫወቻ እና ማረፍያዎች 45 መጋዘንና የመጸዳጃ ክፍሎች ፣ ፋውንቴይን ፣ አምፊ ቴአትር  እና ፕላዛ  አሉት።

ሌላኛዉ ባሻ ወልዴ ችሎት  ጋ የተሰራዉ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያና ገበያ ማዕከል ሲሆን፣  በተመሳሳይ ካፍቴሪያዎች ፣ሱፐርማርኬት ፣ሱቆች ፣ሬስቶራንቶች ፣ ፕላዛ እና 200 የመኪና ማቆሚያ 
በውስጡ  የያዘ ነዉ።
ሁለቱም ማእከላት ዘመናዊ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያና፤ የደህንነት ካሜራ  ተገጥመውለታል ፣ ለህፃናት ፣ለአቅመ ደካምችና አረጋዉያን ምቹ  እና አካታች መሰረተ ልማት ነዉ።

በጥቅሉ ከሜክሲኮ እስከ  ለገሃር እና አፍሪካ ህብረት ዙሪያ ባሉ የተለያዩ  ቦታዎች ላይ 13 የመኪና ማቆሚና 10 ተርሚናሎች እስከ  3769 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ የፓርኪንግ እና ተርሚናል መሰረተ ልማቶች ጭምር ይገኙበታል ።

እነኚህ ለከተማችን እድገት ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች በታለመላቸዉ ጊዜ እና በጀት እንዲጠናቀቁ ሌት ተቀን ለደገፋችሁ አመራሮች ፣ ባለሙያዎችና የየአካባቢዉ ማህበረሰብ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለዉ ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.