የዝምባቡዬ መንግስት የፋይናንስ ሚኒስተር ልዑካን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የዝምባቡዬ መንግስት የፋይናንስ ሚኒስተር ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ በመገኘት የልምድ ልዉዉጥ አደረገ

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር  ሪድዋን በተገኙበት በከተማዋ አጠቃላይ  ዘርፈ- ብዙ የልማት ስራዎች እና የመጡ ለዉጦች ላይ  ለልዑካን ቡድኑ  የልምድ ልዉዉጥ ዉይይት ተደርጓል፡፡

በሁለቱ እህትማማች ሃገራት በተደረገዉ ዉይይት ከተማ አስተዳደሩ ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ መዲናዋ ሃገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መቀመጫ እንደመሆኗ የዜጎችን ህይወት ለመለወጥና  በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ምርጥ ከተማ እንድትሆን በርካታ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸዉና ለዉጦች መመዝገባቸዉ ተገልፃል፡፡

ለእነዚህ ዉጤቶች መሳካትም የመንግስት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እና የህዝቡ የለዉጥ ፍላጎት ወሳኝ ሚና መጫወቱ ተመላክቷል፡፡

የአመራር የመሪነት ብቃት መኖር ፤ግልፅ የጠራና ሊያሰራ የሚችል እቅድና የአሰራር ስርዓት መዘርጋት፤የኮሙኒኬሽን ተግባቦት በመፍጠር ህብረተሰቡን የልማቱ ባለቤት በማድረግ በቅንጅት መስራት፤ተዓማኒነትን ማስረፅ እና በልማቱ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ መቻል፤የከተማዋን የገቢ አቅም በማሳዳግ ሃብትን አሟጦ መጠቀምና ለታለመለት ዓላማ ማዋል፤የስራ ባህል መቀየርና የቴክኖሎጂ አቅምን ማሳደግ፤ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር ለከተማዋ ፈጣን እድገትና ተጨባጭ ለዉጥ መመዝገብ ምክንያት መሆናቸዉ የልዑካን ቡድኑ ልምድ የቀሰሙበት መሆኑ ታዉቋል፡፡

በመጨረሻም ከተማ አስተዳደሩ ላደረገላቸዉ መልካም አቀባበል እንዲሁም ስላካፈላቸዉ ልምድና ተሞክሮ ልዑካን ቡድኑ ምስጋናቸዉን ያቀረቡ ሲሆን  ሁለቱም ሃገራት የሀገራቸዉን እድገት እና የህዝባቸዉን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የነበራቸዉን ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር ልምድ በመለዋወጥ እንደሚሰሩ በተደረገዉ ዉይይት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከዉይይቱ በኋላም የልዑካን ቡድኑ በከተማዋ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን ተዘዋዉረው ጎብኝተዋል ፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.