.png)
ባለፉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ በየደረጃው ባሉ አመራሮች ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ተጠናቋል::
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
አዲስ አበባን የብልፅግና በር!
በአዲስ አበባ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማጠናከር እንደ ሀገር ከነበርንበት የቁልቁለት ጉዞ ለማንሰራራት፣ ባለፉት ሰባት አመታት በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ስኬቶችን አልቆ ለማስቀጠል ፣ ጉለቶችንም በማረም ለታለመለት ሁለንተናዊ ስኬት ለመድረስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለሶስት ቀናት ሲያካሄዱት የነበረውን ውይይት በተሻለ ተነሳሽነት ለላቀ ውጤት ለመትጋት ተግባቦት ላይ በመድረስ አጠናቅቋል።
ሀገራዊ ለውጡ እውን ሲሆን ከተማችን እንዲሁም ሀገራችን የነበሩበት ነባራዊ ሁኔታ ፣ የነበሩ ውስብስብ ችግሮችን በመሻገር ታሪካዊ ስብራቶችን ለመጠገን የተወሰዱ እርምጃዎች ፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች እና በፈተናዎች ውስጥ የተመዘገቡ አንፀባራቂ ድሎች በውይይቱ ላይ ተዳስሰዋል።
ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት የመንግስትን የመፈፀም አቅም ለማሳደግ የተያዘው አቅጣጫ ተግባራዊ እየተደረገ በመሆኑ ተነሳሽነትን ከፍ የሚያደርጉ ስኬቶች በየዘርፉ መመዝገባቸውም በውይይቱ ተመላክቷል።
ለሶስት ቀናት ሲካሄድ በቆየው ውይይትም የአዲስ አበባን ተምሳሌትነት እና የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በቀጣይም የፓርቲያችንን አሻጋሪ እሳቤዎች በቁርጠኝነት ለመፈፀም እንዲሁም ለማስፈፀም ተግባቦት ተፈጥሯል።
ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕያችን አሳታፊ እና አካታች ነው። አመራሩም ፣ አባላትም ፣ ሁሉም ዜጋ በየተሰማራበት ታሪካዊ ኃላፊነቱን በመወጣት አሻራውን ሲያሳርፍ የሀገራችንን ልዕልና የማረጋገጥ ጉዞአችን ይበልጥ ይፋጠናል።
መንግስት በሰላም ስራዎች ላይ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ በመቀጠል ፣ የዜጎችን ሰላም ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየሰራ ሲሆን ፣ በየጊዜው የሚደረጉ መሰል ውይይቶች ደግሞ ወቅታዊ ፣ ሀገራዊ ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ በማስያዝ ጭምር ፣ በፓርቲያችን ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ግልፅነት ፈጥሮ ተልዕኮን በተቀናጀ አግባብ ለመፈፀም የጎላ አበርክቶ እንደሚኖራቸው ይታመናል::
በየደረጃው ያለው አመራርም በአገልግሎት አሰጣጡ ፣ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን በመታገል ፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እና የልማት አርበኛ በመሆን ለሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት ለመትጋት ተነሳሽነት በመፍጠር ለተሻለ ስኬት እንደሚሰሩ አንስተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.