አርባምንጭ በተፈጥሮ ስሪቷ ውብ ናት። በከተማዋ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አርባምንጭ በተፈጥሮ ስሪቷ ውብ ናት። በከተማዋ እየተካሄዱ ያሉ የልማት ሥራዎች በቅርቡ በጎበኘንበት ወቅት የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክትን ተመልክተናል።

 ይኽ ሥራ በመጠነ ርዕዩ ግዙፍ በመሆኑ አርባምንጭ ታላላቅ ጉባኤዎችን እንድታስተናገድ ያስችላታል። ከዚህ ቀደም ከነበረን ምልከታ ሰፋ ብሎ የተከናወነው የኩልፎ ወንዝ ዳርቻ ልማት ለከተማዋ ልዩ መልኮች ተጨማሪ ገጽታ ፈጥሯል።

ወደ አርባምንጭ ጫካ አዳዲስ የመግቢያ መንገዶች የተሠሩ ሲሆን ለተራሮቹ፣ ለውሃው እና ለከባቢው ደኖች መዳረሻ በር ሆነዋል። እነዚህና ሌሎች ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ብዙ ከተሞች ያየናቸው መሻሻሎች የተለያዩ አማራጮች እንዳሉን የሚያሳዩ ያልተጠቀምንባቸውን አቅሞቻችንንም የሚገልጡ ናቸው። ይኽ እድገት በጋራ ጥረቶቻችን ታላላቅ ነገሮችን እንደምናሳካ የሚያመለክት ግልጽ ምልክት ነው።

   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድ (ዶ/ር)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.