የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባዉን አካሄዷል::

ካቢኔዉ በዛሬዉ ውሎዉ በቀረቡት 4 የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ  ውይይት በማድረግ የተለያዩ ዉሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሰረት ፡-
1ኛ ራስን ችሎ የሚለማ ቦታ ዝቅተኛው ስፋትና የፊት ለፊት ገፅታ ርዝመት ( set back)  አተገባበር ጥናት ላይ ተወያይቶ የከተማዋን እድገት ታሳቢ ያደረገ እና የአተገባበር  ምቹነት ታሳቢ ባደረገ የቀረበዉ ጥናት ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

2ኛ በኮሪደር ልማት የለሙ ልዩ ልዩ መሰረተ ልማቶች እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር  ባለስልጣን ለማቋቋም የቀረበዉ  ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ  የማስተዳደር ፣ አገልግሎት የመስጠት፣የመጠበቅ ፣የማስተባበር እና የማቀናጀት ኃላፊነት እንዲኖረው ሆኖ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል፡፡

3ኛ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ አስተዳደር አግባብነት ያለዉ አካል ሳይፈቅድ ፤ የተያዙ ይዞታዎች አገልግሎት የመስጠት ጊዜን  ለማራዘም በቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

4ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች እና የኢንዱስትሪ ልማት ተቋማት ላይ ለመሳተፍ የቀረበ የመሬት ጥያቄ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.