የአዲስ አበባ የኮሪደርና የወንዝ ዳር ልማቶች የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ የኮሪደርና የወንዝ ዳር ልማቶች የማንሰራራት ዘመን አብሳሪዎች ናቸው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

የአዲስ አበባ የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማቶች ለመዲናችን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈቱ፣ ደረጃውን የጠበቀ የክትመት ንጋት እና የማንሰራራት ዘመን አብሳሪዎች ናቸው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ደረጃቸውን የጠበቁ ከተሞች የሀገራት ስልጣኔ፣ የተፈጥሮ ሚዛን ጥበቃ፣ የሕዝቦች የእሳቤ ከፍታ አድማስ እና አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴዎች የሚነበብባቸው ገጾች ናቸው ብለዋል።

አዲስ አበባ በልጆቿ ብርቱ ክንዶች እየለማችና እየደመቀች፣ በነዋሪዎቿ ትጋት እየፈካች እና እየተዋበች በተግባር ስሟን እየሆነች ያለች ከተማ ናት ሲሉ ገልጸዋል።

የሀገራችንና የአፍሪካ መዲናችን የውበት ብቻ ሳይሆን የቀልጣፋ አገልግሎት፤ የመዝናኛ ብቻ ሳይሆን የምቹ ኑሮ፤ ከዚህም ባለፈ አጠቃላይ የሀገራችን ፈጣን ልማት የሚቃኝባት የዕድገታችን ማሳያ ናት ነው ያሉት።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.