"ጤናማ፣ በሚገባ የተጠበቁ የወንዝ ዳርቻዎች የከ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ጤናማ፣ በሚገባ የተጠበቁ የወንዝ ዳርቻዎች የከባቢ ሥርዓትን እና የውሃ ጥራትን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰብን የኑሮ ደህንነት የሚያሻሽሉ እና የከተሞችን ለፈተና አለመበገር የሚያጠናክሩ ደማቅ ሕዝባዊ ሥፍራዎችን ይፈጥራሉ።

ዛሬ ከሰዓት ከብልጽግና ምክር ቤት ስብሰባ በኋላ የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት የሥራ ሂደትን በጋራ ተመልክተናል። ይኽ ሥራ አሁን በተያዘው ምዕራፍ በአምስት ክፍለ ከተሞች የሚዘልቅና 21.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው። ፕሮጀክቱ በጥቂቱ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መንገፍ፣ ሕዝባዊ ፕላዛዎች፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች፣ ሱቆች እና አምፊቴአትሮች የተካተቱበትም ነው። 

ከዚህ ግዙፍ ሥራ አላማዎች መካከልም የወንዞች ብክለትን ማስወገድ፣ የከተማዋን የጎርፍ ተጋላጭነት መቀነስ፣ ሕዝባዊ መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን ቁጥር መጨመር እና የሥራ እድል መፍጠር ይገኙበታል። 

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ አካባቢያችንን ከመጠበቅ ባሻገር ለአዲስ አበባ ደማቅ እና ዘላቂ የወንዝ ዳርቻዎችን በማስገኘት የከተማዋን ኢኮኖሚ እና የኑሮ ደረጃ ከፍ ያደርጋል"።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመ(ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.