
የዋና ጸሀፊው ንግግርና እንድምታው፡
በተርክሜኒስታን እየተካሄደ ባለው 3ኛው የተባበሩት መንግስታት በማደግ ላይ ያሉ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ጉባኤ ላይ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ያደረጉት ንግግርም ሆነ ያሳዩት አቋም አርቆአሳቢው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቢይ አህመድ(ዶ/ር) በቁጭት እያራመዱት ካለው አቋም ጋር የሚጣጣም ነው፡፡
በመሆኑም ንግግራቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሎም ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ እያራመደችው ያለው አቋም ትክክለኛ ከመሆንም ባለፈ አለም እየተቀበለው የመጣ ዕውነታ ስለመሆኑ ሁነኛ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡
የዋና ጸሃፊው ንግግር በዋናነት:-
👉 አሁን ያለው የአለም የንግድ ስርዓት ከዓለም ህዝብ 7 በመቶ የሚሆነውን የያዙና የባህር በር የሌላቸውን ከ30 በላይ ሀገራት ያገለለ በመሆኑ ብቻ ፍትሃዊነት የጎደለው መሆኑን::
👉የባህር በር አልባ መሆን በታሪክ አጋጣሚ በጥቂት ሀገራት ላይ የወደቀ ዱብዳ እንጂ እርግማን አለመሆኑን:
👉አሁን ያለው ኢ-ፍትሀዊነት የነገሰበት የአለም የንግድ ስርዓት የነዚህን ሀገራት ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ታሳቢ ባደረግ መልኩ መዋቅራዊ ለውጥ ማድረግ ይገባዋል ሲባል የመብት ጉዳይ እንጂ እንደ ቸርነት ሊታይ የማይገባው መሆኑ፡
👉የባህር በር አልባነት የነዚህ ሀገራት የመጨረሻ ዕጣፈንታ መሆን እንደሌለበት ብሎም መጪው የሀገራቱ ዕድል በዚህ ሊወሰን በፍጹም እንደማይገባው፤
👉የባህር በር አልባ በመሆናቸው ብቻ በነዚህ ሀገራት ላይ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ ኢኮኖሚየዊ ጫና/ተግዳሮት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየከፋ መምጣቱን፣ የሀገራቱን የመልማት ዕድል እያቀጨጨ መሆኑ እና ቆም ተብሎ ሊታሰብበት እንደሚገባ፤
👉የአለማችን የንግድ ስርዓት ፍትሀዊ፣አሳታፊ ብሎም በአጋርነት መንፈስና መተሳሰብ ላይ የታነጸ መሆን እንደሚገባው ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነበር ማለት ይቻላል::
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ በመደገፍ ከሀገራቱ ጎን እንደሚቆም ዋና ጸሃፊው ቃል መግባታቸው ደግሞ ትልቅ እምርታ ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ይህ ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.