የደንብ ማስከበር ተግባራቸውን በመወጣት ላይ በነ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የደንብ ማስከበር ተግባራቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት ላይ የድብደባ ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ መሆኑን የን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ጀሞ መስታወት ፋብሪካ አካባቢ ሲሆን ተከሳሾች ዮሀንስ ከበደ፣ ሠዒድ ሠይፉ፣ እስማኤል ሱልጣን፣ ሃይረዲን ሽፋ፣ ፈጅሩ ሱልጣን፣ ባህሩ ራህመቶ፣ ሚነወር ሀይሉ፣ ሀይልዬ ጀማልና አስማረ አለሙ የተባሉ ሲሆኑ ካልተያዙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በመሆን በእግረኛ መንገድ ላይ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ንግድ በማከናወን ላይ ሳሉ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት የሆኑት ማቱሳላ ማዶሬና አቡሽ ሽጉጤ ድርጊቱን ለመከላከል ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ አባሪ ተባባሪ በመሆን አባላቱን በድንጋይና በእርግጫ ተረባርበው የድብደባ ወንጀል መፈጸማቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ በወቅቱ ድርጊቱን ፈጽመው ቢሰወሩም በክ/ከተማው ፖሊስ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ፖሊስ ገልጾ በፈጸሙት የወንጀል ድርጊትም ተገቢውን ምርመራ የማጣራትና ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረቱን መቀጠሉንም ገልጿል።

በጎዳና ላይ የሚደረጉ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች የእግረኛና የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በማወክ ዜጎችን ለመንገድ ትራፊክ አደጋ ተጋላጭ ከማድረጉም ባሻገር ጤናማ የንግድ እንቅስቃሴን የሚጎዳ መሆኑ እየታወቀ ይህንንም ድርጊት ለመከላከል የተሠማሩ የጸጥታ አካላት ላይ ትንኮሳ መፈጸምና ለህግ ተገዢ ያለመሆን ተጠያቂነትን የሚያስከትል ድርጊት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሳስባል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.