በመጪው ሀሙስ በጋራ ታሪክ እንስራ!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመጪው ሀሙስ በጋራ ታሪክ እንስራ!

በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያ አረንጓዴ እና ለፈተና የማይበገር ነገዋን ለመገንባት ለምታደርገው ጥረት እንደገና ትነሳለች። ነገ ከንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራችን አካል የሆነውን በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል አላማን ለማሳካት እንነሳለን። ከፍ ያለ ግብ ነው። ግን ጥንካሬያችንን፣ አንድነታችንን እና ለሕዝባችን ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል።

ይኽ ችግኝ ከመትከል በላይ ነው። ትንሽ ትልቅ፣ የከተማ የገጠር ሳንል ዜጎች ሁሉ አካባቢያችን እንዲያገግም፣ የውሃ ምንጮቻችን እንዲጠበቁ፣ የኑሮ ሁኔታችን እንዲሻሻል እንዲሁም ለመጪው ትውልዶች ዘላቂነት ያለው ነገን ለማረጋገጥ የምንሳተፍበት ተግባር ነው።

ሁላችሁም በዚህ ታላቅ ሥራ እንድትሳተፉ እና እንድታስተባብሩ አሳስባለሁ። በጋራ ጠንካራ ዛፎችን ብቻ ሳይሆን ጠንካራ እና የበለጠ አረንጓዴ የሆነች ኢትዮጵያን እናሳድጋለን።

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድ (ዶ/ር)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.