
"በመትከል ማንሰራራት "በሚል መሪ ቃል ዛሬ ማለዳ ከኮሙኒኬሽን እና ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በቀበና ወንዝ ዳርቻ ችግኝ ተክለናል
የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በኢትዮጵያውያን በጎ የሆነን ሀሳብ የምታሰርፁ ናችሁና እና አሁንም ስራችሁን እንድታጠናክሩ እላለሁ ።
ዛፍ መትከል የዛሬ ብቻ ሳይሆን የነገም ተስፋችን እንዲሁም የምግብ ዋስትናችንን ለነገው ትውልድ የምናረጋግጥበት በመሆኑ በዛሬው መረሀ ግብር የተሳተፋችሁ ከመትከል ባሻገር መልካም ሀሳብ የምታሰርፁ ናችሁና ችግኞችን ከመትከል ባሻገር ትውልድን የማነፅ ስራ እንድትሰሩ አደራ እላለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.