.png)
ዛሬ የህፃናትን የፈጠራ እና የማሰላሰል አቅም የሚጨምሩ በጨዋታ መልክ ለማስተማር የሚያግዙ በርካታ መጫወቻዎች ከሎጎ ፋዉንዴሽን በክሊቲን ሐልዝ አክሰስ ኢንሼቲቭ በኩል ተበርክቶልናል ።
በከተማችን የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ፕሮግራምን ዋነኛ የትዉልድና የአገር ግንባታ ምሶሶ አድርገን በስፋት እየሰራንበት እንገኛለን ።
ይህ ፕሮግራም በክህሎት የዳበረ፣ በፈጠራ የጎለበተ አካባቢዉን በሚገባ የተረዳና ለሚገጥሙት ፈተናዎች አስቀድም ሳይንሳዊ መፍትሔ የሚያበጅ ጠንካራና አገር ወዳድ ትውልድ ለመገንባት ያስችላል ።
ፕሮግራሙ ተግባራዊ ማድረግ ከተጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆንም በርካታ አገራት ከወዲሁ ውጤቱን በመረዳት ልምድ እየቀሰሙበት እና እየደገፉት ይገኛል ።
ስጦታዎቹ የአዕምሮ እድገት ውስንነትና የአካል ጉዳት ያለባቸውን ህፃናት ጭምር ያማከለ በመሆኑ አስተባባሪዎቹን ከልብ አመሰግናለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.