.png)
ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ በጥራት በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርጓል ::በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተገነቡ 28 የጤና ፕሮጄክቶች መካከል በዛሬው እለት 22 የጤና ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 2 ጤና ጣቢያን ጨምሮ ግንባታቸው የተጠናቁ የጤና ተቋማት መርቆው የከፈቱት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ረድዋን ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ በጥራት በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል ።
አቶ አብዱልቃድር አክለው የከተማ አስተዳደሩ የማህበረሰቡን የልማትና የአግልግሎት ጥያቄ ለመመለስ ቁርጠኛ አቋም ይዘው ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረው በጤና ዘርፉ ነዋሪው አገልግሎት በቅርበት እንዲያገኝና አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጡ ጤና ጣቢያዎች በመገንባት እንዲሁም ማስፋፊያና የማዘመን ስራዎች መስራቱን ገልፀዋል።
ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው 2017 በጀት አመት በጤና ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማሻሻል ውጤታማ ስራዎችን መሰራታቸውን ጠቅሰው የአካባቢው ማህበረሰብ የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ የቆየው የጤና አገልግሎት በአጭር ጊዜ በጥራትና ዘመናዊ በሆነ መልኩ በማጠናቀቅ የለህዝቡ ምላሽ የሰጠ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.