.png)
በየካ ክፍለ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ የጤና ተቋማት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ!
በበጀት ዓመቱ ከተጀመሩት 28 የጤና ፕሮጀክቶች 22ቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርጏል::
በምክትል ከምቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እንደገለፁት የህዝባችንን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፍ በርካታ ፕሮጀክቶችን ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ የህዝባችንን ተጠቃሚ እያረጋገጥን እንገኛለን። በዛሬው ዕለትም የሚመረቁት የጤና ተቋማት ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሲሆን በጤናው ዘርፍ እምርታዊ ለውጥ ከማምጣት ባለፈ የታካሚዎችን ምቹና አስፈላጊው ግብዓት በማሟላት ወደ ስራ በማስገባት ቃልን ወደ ተግባር የቀየርንባቸው ናቸው ብለዋል።
አክለውም ከተማ አስተዳደሩ የጤና መሰረተ ልማትን ለማሟላት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝና ጥራት ያለው አገልግሎት ለህብረተሰባችን ለመስጠት በበጀት ዓመቱ ከተጀመሩት 28 የጤና ፕሮጀክቶች 22ቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን አክለዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በበጀት ዓመቱ በመንግስት ካፒታል እና በህብረተሰብ ተሳትፎ በርካታ ፕሮጀክቶች ሰርቶ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን በመግለፅ ፕሮጀክቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለተባበሩ አካላትን አመስግነዋል።
ለረጅም ዓመት የመልካም አስተዳደር ችግር የነበረው የየካ ወረዳ 03 G+4 ጤና ጣቢያ እና ወረዳ 12 G+4 ጤና ጣቢያ የማስፋፊያ ህንፃ ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸው የነዋሪዎችን ጥያቄ ከመመለስ ባለፍ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለህብረተሰባችን የሚሰጡ መሆኑን እና የሆስፒታሎችን ጫና የሚያቃልል መሆኑን አብራርተዋል።
በመጨረሻም ከፍተኛ አመራሮቹ በየካ ቤላ ጤና ጣቢያ ቅጥር ግቢ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.